የብላቴ ልዩ ሀይል ዘመቻ መምሪያ ወታደሮችን እያስመረቀ ነው

161

ብላቴ፣ መስከረም 3/2014 (ኢዜአ) የብላቴ ልዩ ሀይል ዘመቻ መምሪያ መሰረታዊ ስልጠና የወሰዱ ወታደሮችን እያስመረቀ ነው።

መምሪያው ከመላ ሀገሪቱ የተውጣጡና በብላቴ መሰረታዊ ስልጠና ያጠናቀቁ ምልምል ወታደሮችን ዛሬ እያስመረቀ ነው።

የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ ደስታ ሌዳሞ በስነ ስርአቱ ላይ በክብር እንግድነት ተገኝተው ምልምል ወታደሮችን እያስመረቁ ነው።

የልዩ ዘመቻዎች ሀይል ማሰልጠኛ አዛዥ ኮሎኔል ዋለልኝ ታደሰ  ለኢዜአ እንዳሉት ተመራቂ ወታደሮች በቆይታቸው የአካል ብቃት፣ የተኩስ፣ የሰልፍና ሌሎች መሰረታዊ የውትድርና ስልጠና የተሰጣቸው ናቸው ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም