በምስራቅ ሐረርጌ በሰላማዊ ሰዎች ላይ በተፈጸመ ጥቃት የ41 ሰዎች ህይወት አለፈ

96
ሐረር ነሃሴ 8/2010 በምስራቅ ሐረርጌ ዞን መዩ ሙሉቄ ወረዳ በታጣቂዎች በተከፈተ ተኩስ የ41 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 20 ሰዎች ላይ ከባድና ቀላል የመቁሰል አደጋ መድረሱን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ። በመምሪያው የመንግስት ኮሚዩኒኬሽን ዲቪዥን ኃላፊ ኮማንደር ስዩም ደገፉ እንደገለጹት ከትላንት በስቲያ ጉዳቱ የደረሰው”በሶማሌ ክልል ልዩ ኃይል ታጣቂዎች”በድንገት በተከፈተ ተኩስና በተወረወረ የእጅ ቦምብ ነው። በጥቃቱ ህይወታቸውን ካጡት መካከል አንዱ የፖሊስ ሰራዊት አባል ሲሆን ሌሎች ሰላማዊ የአካባቢው ነዋሪዎች መሆናቸውን አስታውቀው የመቁሰል አደጋ የደረሰባቸው ወገኖች ደግሞ በጋራሙለታ ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅትም ህብረተሰቡና የጸጥታ አካላት ባደረጉት ርብርብ አካባቢውን ወደ ነበረበት መረጋጋት መመለስ መቻሉን ኮማንደር ስዩም ጠቁመዋል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም