የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመከላከያ ሠራዊት 60 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ - ኢዜአ አማርኛ
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለመከላከያ ሠራዊት 60 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ
61
አዲስ አበባ፣ ጳጉሜ 03 ቀን 2013 (ኢዜአ) የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ አባላት ለአገር መከላከያ ሠራዊት 60 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አበረከቱ።
ድጋፉን የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ፕሮፌሰር ጣሰው ወልደሃና አስረክበዋል።
ድጋፉን የተረከቡት የመከላከያ ሚኒስትር ዶክተር ቀነዓ ያደታ የዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ አባላት ላደረጉት ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል።
የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እስካሁን በአይነትና በገንዘብ 240 ሚሊዮን ብር ድጋፍ ማድረጋቸውንም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያዊያን ለአገሩና ለሕዝቡ መስዋዕትነት እየከፈለ ላለው የመከላከያ ሠራዊትና ለጸጥታ ሀይሎች በገንዘብ፣ በሙያና በአይነት የተለያዩ ድጋፎችን ማድረጋቸውን ቀጥለዋል።