ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ዱከም የሚገኘውን የኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን ጎበኙ

72
አዲስ አበባ ነሃሴ 7/2010 የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት ዶክተር ሙላቱ ተሾመ ዱከም የሚገኘውን የኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞን ጎበኙ። ፕሬዚዳንቱ በኢንዱስትሪ ዞኑ ውስጥ የሚገኙ የወረቀት፣የመድሃኒት፣ የጂንስ ልብስ፣ የብረታ ብረት፣ የአልሙኒየምና ጫማ ፋብሪካዎችን ነው የጎበኙት። ጉብኝታቸውን ሲያጠናቅቁ በኢንዱስትሪ ዞኑ ከሚገኙ ባለሀብቶች ጋር ውይይት አድርገዋል። ኢትዮጵያ ከግብርና መር ወደ ኢንዱስትሪ መር ለምታደርገው የኢኮኖሚ ሽግግር የኢስተርን ኢንዱስትሪ ዞንን ጨምሮ በርካታ የኢንዱስትሪ ዞኖችን ከአገሪቷ የልማት ኮሪደሮች አኳያ በመገንባት ላይ ትገኛለች።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም