ኮርፖሬሽኑ ለመከላከያ ሰራዊት 4 ሚሊየን ብር የገንዘብ ድጋፍ አደረገ

56

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 27/2013(ኢዜአ) የኢትዮጵያ የግብርና ስራዎች ኮርፖሬሽን ለአገር መከላከያ ሰራዊት 4 ሚሊየን ብር ድጋፍ አደረገ።

የተቋሙ ሰራተኞችም ”ደማችን ለመከላከያችን” በሚል መሪ ሃሳብ ለሰራዊቱ ደማቸውን ለግሰዋል፡፡

የተቋሙ ሰራተኞች በዛሬው እለት ደማቸውን የለገሱ ሲሆን ለአገራቸው ህልውና ሲሉ ከድጋፍ በተጨማሪ የትኛውንም መስዋእትነት ለመክፈል ዝግጁ መሆናቸውን ገልጸዋል።

የአገር ሉአላዊነትን ለማስከበር ከአገር መከላከያ ሰራዊት ጎን በመቆም ድጋፍና እገዛቸውን አጠናክረው እንደሚቀጥሉም አረጋግጠዋል፡፡

ሀገራዊ ለውጡ ለማደናቀፍ እና ያለፈውን ስርአት ለመመለስ የሚፍጨረጨረውን የአሸባሪውን ሃይል አፍራሽና ከፋፋይ ተልዕኮ በማክሸፍ ለአገራቸው ህልውና እንደሚቆሙም ሰራተኞቹ አረጋግጠዋል።

የአካባቢያቸውን ሰላም ለመጠበቅም ከምንጊዜውም በላይ ዝግጁ ሆነው እንደሚሰሩ ገልጸዋል፡፡

የህወሃት አሸባሪ ቡድን በከፈተው ጦርነት ለተፈናቀሉ ዜጎች የምግብና አልባሳት ድጋፍ እናደርጋለንም ብለዋል።

የኮርፖሬሽኑ ሰራተኞች የግብርና ዘርፍ ምርት እና ምርታማነትን ለማሳደግ በትኩረት እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

“ኢትዮጵያን ለማዳን እዘምታለሁ፤ የትም፣ መቼም፣ በምንም!” በሚል መሪ ሃሳብ ዜጎች የድርሻቸውን በመወጣት ላይ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም