የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት ጉባዔ 8 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በጀት አጸደቀ

101

ሰመራ፣  ነሐሴ 24 ቀን 2013 (ኢዜአ) የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግሥት ምክር ቤት 11ኛ መደበኛ ጉባዔ ለ2014 የሥራ ዘመን ማስፈጸሚያ 8 ነጥብ 8 ቢሊዮን ብር በጀት አጸደቀ።

የምክር ቤቱ ጉባዔ በጀቱን  ያጸደቀው በቀረበው ረቂቅ የበጀት አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ ነው።

የክልሉ ፋይናንስና ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሃላፊ አቶ መሐመድ ሐሰን ለምክር ቤቱ እንዳብራሩት፤ በጀቱ የፌዴራል መንግሥት ድጎማ፣ የውጭ እርዳታና የክልሉ የውስጥ  ገቢ ታሳቢ ተደርጎ የተዘጋጀ ነው።

በጀቱ የክልሉን የጤናና ውሃ  ችግሮችን ለማቃለል እንዲሁም የሰላምና ጸጥታ ተቋማትን ለማጠናከር ትኩረት ማድረጉም ተመልክቷል።

በየደረጃው ለሚገኙ የክልሉ መንግሥት አስፈጻሚዎች ለመደበኛና ካፒታል በጀት እንዲሁም ለዘላቂ የልማት ግቦች ማስፈጸሚያም  እንደሚውልም ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም