በሃይቲ በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ የሟቾች ቁጥር 2 ሺህ አልፏል

113

ነሀሴ 12/2013 (ኢዜአ) ሀይቲ ውስጥ ባለፈው ሳምንት በደረሰው የመሬት መንቀጥቀጥ ቢያንስ 1 ሺህ 941 ሰዎች መሞታቸው ታውቋል በአሁኑ ሰአት ቀደም ሲል ከነበረው ቁጥር ከ 500 በላይ መጨመሩን ባለስልጣናት ተናግረዋል።

ከ 7.2 መጠን ያለው የመሬት መንቀጥቀጥ ተከትሎ ወደ 10 ሺህ የሚጠጉ ሰዎች የመቁሰልና መሰል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን ብዙዎች አሁንም የገቡበት አልታወቀም ነው የተባለው፡፡

በወቅቱ የጣለው ከባድ ዝናብ የነብስ አድን ስራው አስቸጋሪ እንዲሆን አድርጎታል ተብሏል፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በአሁኑ ወቅት ወደ 500, ሺህ የሚጠጉ ሕፃናት መጠለያ ፣ ንፁህ ውሃ እና ምግብ ለማግኘት መቸገራቸውን ጠቅሷል፡፡

በሀገሪቱ ውስጥ የተባበሩት መንግስታት የሕፃናት መርጃ ድርጅት (ዩኒሴፍ) ተወካይ ብሩኖ ማይስ “በመሬት መንቀጥቀጡ ምክንያት ሁሉንም ነገር ያጡ የሄይቲ ቤተሰቦች አሁንም በጎርፉ ምክንያት እግሮቻቸውን በውኃ ውስጥ ነክረው እየኖሩ ነው” ብለዋል።

አደጋው የሄይቲ ደቡብ-ምዕራብ በተለይም በሌሴስ ከተማ ዙሪያ የከፋ ጉዳት እንዳደረሰበት ተነስቷል፡፡

የከተማው ነዋሪ ማጋሊ ካዴት “ትናንት ምሽት በቤተክርስቲያኑ አቅራቢያ መጠለያ አግኝቼ ነበር ፣ ነገር ግን መሬቱ እንደገና ሲንቀጠቀጥ በሰማሁ ጊዜ ወደዚህ ለመመለስ ሮጫለሁ” ሲል ለኤፍ.ፒ.ኤስ የዜና ወኪል ተናግረዋል፡፡

አያይዞም በከተማዋ ስራቸውን በአግባቡ ያልሰሩ ባለስልጣናት መኖራቸው በአስተያየታቸው አክለዋል፡፡

የጤና ባለሙያዎች በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን ለመርዳት ሲሯሯጡ በአንዳንድ ሆስፒታሎች ከአቅማቸው በላይ እንደሆነባቸው የቢቢሲ ዘገባ ያመለክታል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም