የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አስተዳደር አዲስ አፈ ጉባኤ ሹመት አጸደቀ

3159

አዲስ አበባ ነሀሴ 4/2010 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አዲስ የአፈ ጉባኤ ሹመት አጸደቀ።

ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ በምክትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ ከቀረቡት አዲስ የካቢኔ ሹመቶች በተጓዳኝ የአዲስ አፈ ጉባዔ ሹመት አጽድቋል።

የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ኃላፊ ሆነው በተሾሙት የቀድሞ አፈ ጉባዔ ዶክተር ታቦር ገብረመድህን ቦታ ላይ ወይዘሮ አበበች ነጋሽን አፈ ጉባዔ አድርጎ ሾሟል።

ምክር ቤቱ ሁለት የተጓደሉ የምክር ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ሹመትም አጽድቋል።