የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አዲስ የካቢኔ አባላት ሹመትን አፀደቀ

175
አዲስ አበባ ነሃሴ 4/2010 የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት አዲስ የካቢኔ አባላት ሹመትን አፀደቀ በዚህ መሰረት፦
  1. ወይዘሮ አልማዝ አብርሃ የሴቶችና ህፃናት ጉዳዮች ቢሮ ሓላፊ
  2. ወይዘሮ ፍሬህይወት ተፈራ የፍትህ ቢሮ ሓላፊ
  3. አቶ ጀማሉ ጀምበር የወጣቶችና ስፖርት ጉዳይ ቢሮ ሓላፊ
  4. አቶ ሺሰማ ገብረስላሴ የገቢዎች ባለስልጣን ሓላፊ
  5. ዶክተር ፍረህይወት ገብረሂወት የፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ ሓላፊ
  6. አቶ አሰፋ ዮሃንስ የቴክኒክና ሙያ ቢሮ ሓላፊ
  7. አቶ ኤርሚያስ ኪሮስ የኢንዱስትሪ ቢሮ ሓላፊ
  8. አቶ አብዱልፈታህ ዮሱፍ የንግድ ቢሮ ሓላፊ
  9. አቶ ፎኢኖ ፎላ የፋይናንስ ኢኮኖሚ ልማት ቢሮ ሓላፊ
10.ኢንጂነር ዮናስ አያሌው የኮንስትራክሽን ቢሮ ሓላፊ
  1. አቶ ሽመልስ እሸቱ የመሬት ልማት ማኔጅመንት ቢሮ ሓላፊ
  2. አቶ ደረጀ ፍቃዱ የፕላን ኮሚሽን ኮሚሽነር
  3. አቶ ዘውዱ ቀፀላ የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ
  4. ዶክተር ዮሃንስ ጫላ የጤና ቢሮ ሓላፊ
  5. አቶ ንጋቱ ዳኛቸው የጥቃቅንና አነስተኛ ቢሮ ሓላፊ
  6. ኢንጅነር ሰናይት ዳምጠው የቤቶች ልማት ቢሮ ሓላፊ
  7. አቶ ነብዩ ባዬ የባህልና ቱሪዝም ሓላፊ  ሲሆኑ ምክር ቤቱ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ ሽመቶቹን አፅድቋል።
ከዚህ በተጨማሪ ምክር ቤቱ የተሻሻለውን የአስፈፃሚና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎት አካላት ረቂቅ አዋጅን አፅድቋል። በዚህ መሰረት በነባር አዋጅ ቁጥር 35/2004 የነበረው የወረዳ ዋና ሥራ አስፈፃሚና ምክትል ሥራ አስፈጻሚ የአሿሿም ሁኔታና የምክትል ሥራ አስፈፃሚ የሥራ ተግባርና ሓላፊነትን ያላካተተ ነበር። በዚህም አንደኛ "የወረዳ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ ከወረዳ ምክር ቤት አባላት ውስጥ ወይም ከዛ ውጪ ሊመረጥ ይችላል" ሁለተኛ ደግሞ "የወረዳ ምክትል ሥራ አስፈፃሚ የሥራ ዘመን የምክር ቤቱ የሥራ ዘመን ይሆናል ሆኖም በራሱ ፍቃድ ሲለቅ ወይም በምክር ቤቱ ከሓላፊነት ሲታገድ የሥራ ዘመኑ ሳያልቅ ከሓላፊነት ሊሰናበት ይችላል" የሚል ሐሳብ አካቶ ነባሩን አዋጅ አሻሽሏል።  
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም