ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመራርና ሰራተኞች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለህልውና ዘመቻው ድጋፍ እንዲውል ወሰኑ

92

ባህርዳር፤ ነሐሴ 6/2013 (ኢዜአ) የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት አመራሮችና ሰራተኞች ለህልውና ዘመቻው የአንድ ወር ደመወዛቸውን ከ30 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ እንዲውል ወሰኑ።
የጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ  ታዘባቸው ጣሴ ዛሬ  በሰጡት መግለጫ፤ አመራሮቹና ሰራተኞቹ  ደመወዛቸውን ለመስጠት የወሰኑት የሀገር ህልውናን ለማስጠበቅ በግንባር እየተዋደቁ የሚገኙ የጸጥታ አካላትን ለመደገፍ ነው ብለዋል።

የህልውና ትግሉን በድል ለመወጣት ሁሉም ኢትዮጵያዊ አቅም ያለው ግንባር ድረስ በመሰለፍ፣ ገንዘብ ያለው በገንዘቡና እውቀት ያለው በጥበቡ የዜግነት ግዴታውን እንዲወጣ የሚያስገድድ ነው።

በዚህም ከክልል እስከ ወረዳ የሚገኙ ዳኞች፣ ሰራተኞችና አመራሮች የአንድ ወር ደመወዛቸውን ከ30 ሚሊዮን 486 ሺህ ብር  በላይ ድጋፍ ለማድረግ መወሰናቸውን አስታውቀዋል።

በተጨማሪም  ከ110 ኩንታል በላይ በሶ በማዘጋጀት ለጸጥታ ሀይሎች ስንቅ እንዲሆን  ለመላክ እያዘጋጁ መሆኑን አስረድተዋል።

በቀጣይም ተመሳሳይ ድጋፎች ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የገለጹት  የህዝብ ግንኙነት ሃላፊው  የህልውና ዘመቻውን ግንባር ድረስ ሂደው ለመቀላቀል ሰራተኞች ወታደራዊ ስልጠና እየወሰዱ ነው ብለዋል።

እንዲሁም የፍርድ ቤቱ አሽከርካሪዎች ከነተሽከርካሪዎቻቸው ግንባር ላይ በመሄድ ሀገራዊና ክልላዊ ግዴታቸውን እየተወጡ መሆናቸውን አመላክተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም