በሻሸመኔ የአሸባሪውን ህወሃት ቡድን የሚቃወምና የሀገር መከላከያን የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ እየተካሄደ ነቅው

70

ሀዋሳ ሐምሌ 18/2013 (ኢዜአ) ከምእራብ አርሲ ዞንና ከሻሸመኔ ከተማ የተውጣጡ ነዋሪዎች አሸባሪውን ህወሃት ቡድን የሚቃወምና የሀገር መከላከያን የሚደግፍ ህዝባዊ ሰልፍ በሻሸመኔ ከተማ እያካሄዱ ነው

ነዋሪዎቹ  ከማለዳው አንስተው ወደ ሻሸመኔ ስታዲዮም በመትመም ለመከላከያ ሰራዊት ድጋፋቸውን እየገለጹና አሸባሪውን ህወሃት እያወገዙ ነው።

የሠልፉ ተሳታፊዎች ከሀገር መከላከያ ሠራዊት ጎን እንደሚቆሙና በሚደረጉ ድጋፎች ሁሉ እንደሚሳተፉ ድምፃቸውን እያሰሙ ነው፡፡

ነዋሪዎቹ ሰራዊቱ የሉአላዊነታችን ምልክት ነው፣ ኢትዮጵያን ማፍረስ አይቻልም፣ የሀገራችን ዳር ድንበር በታሪክ እንደተጠበቀ ሁሉ ፀንቶ ይቆያል፣ ሕዳሴው ግድብ ሁለተኛ ዙር የውኃ ሙሌት በስኬት መከናወኑ የሰላማችን አርማ ነው የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን እያሰሰሙ ነው።

መከላከያ ለህዝቦች ደህንነትና ለህገ መንግስቱ የቆመ ሰራዊት ነው፣ መከላከያ ሰራዊት የኢትዮጵያውያን የስነልቦና ከፍታ ማሳያ ነው፣ እኛ የጀግናው መከላከያ ሠራዊታችን ደጀን ነን፣ ኢትዮጵያ አሸንፋለች ሰላሟንምን ትጠብቃለች ሲሉም  ድጋፋቸውን እየገለጹ ነው።

ኢትዮጵያ በጀግኖቿ አፈራ አታውቅም፤ የትግራይ ህጻናት ትምህርት እንጂ መሣሪያ መታጠቅ የለባቸውም፤ ከትግራይ ህጻናት ትከሻ ላይ መሳሪያ ይውረድ በሚል ህወሀትን በማውገዝ ላይ ናቸው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም