ሚኒስቴሩ በአሶሳ ለአቅመ ደካሞች ለሚገነባው የመኖሪያ መንደር 10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

1180

አሶሳ፤ ሐምሌ 17 ቀን 2013 (ኢዜአ) የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስቴር አሶሳ ከተማ ለአቅመ ደካሞች ለሚገነባው የመኖሪያ መንደር የ10 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ፡፡

ድጋፉን የማዕድንና ነዳጅ ሚኒስትር ኢንጂነር ታከለ ኡማ ለቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ርዕሰ መስተደድር አቶ አሻድሊ ሐሰን ዛሬ አስረክበዋል፡፡

ድጋፉ የወርቅና የእምነበረድ መገኛ በሆነው ክልሉ  ለ20  አቅመ ደካሞች መኖሪያ ቤት ግንባታ እንደሚውል ተገልጿል፡፡

የመንደሩ ግንባታ በአንድ ወር ተጠናቅቆ ለተጠቃሚዎች እንደሚተላለፍ ተመልክቷል፡፡

አቶ አሻድሉ ሚኒስቴሩ ላደረገው ድጋፍ ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ርዕሰ መስተዳድሩ በዚሁ ወቅት የክልሉን የክረምት በጎ ፈቃድ አገልግሎት ማስጀመሪያ መርሐ ግብር አስጀምረዋል፡፡

በሥነ-ሥርዓቱ ላይ የተካፈሉ የፌደራልና የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች በአካባቢው ችግኞችን ተክለዋል፡፡