የእንጅባራና ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲዎች እንዲሁም የደሴ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎችን እያስመረቁ ነው

95

እንጅባራ/ ደብረ ማርቆስ/ደሴ ፤ሐምሌ 17/2013(ኢዜአ) የእንጅባራና ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርስቲዎች እንዲሁም የደሴ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠኗቸውን 5 ሺህ 236 ተማሪዎች እያስመረቁ ነው።


እንጅባራ ዩኒቨርስቲ ለሁለተኛ ጊዜ በአምስት ኮሌጆች ሥር ባሉ 24 የትምህርት ክፍሎች በመጀመሪያ ዲግሪና ከፍተኛ ዲፕሎማ ያስተማራቸውን 1ሺህ 74 ተማሪዎች ያስመርቃል፡፡

የግብርና ሳይንስ፣ ቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ ተፈጥሮ ሳይንስ ቀመር፣ እንዲሁም በትምህርትና ስነ ሰብዕ ሳይንስ ተመራቂዎቹ ከሰለጠኑባቸው የትምህርት መስኮች መካከል ይገኙበታል።

ከተመራቂዎቹም 426 ሴቶች መሆናቸው በስነ-ስርዓቱ ላይ ተገልጿል።

በተመሳሳይ ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ በመደበኛ፣ በማታውና በክረምት መርሃ ግብር በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ያሰለጠናቸውን 3 ሺህ 712 ተማሪዎችን እያስመረቀ ይገኛል።

 ከአጠቃላይ ተመራቂዎችም አንድ ሺህ 336   ሴቶች እንደሆኑ ተመልክቷል።

በሌላ በኩል የደሴ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በዲፕሎማ ያሰለጠናቸውን 450 የጤና ባለሙያዎች እያስመረቀ ነው።

በተቋማቱ የምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ የፌዴራልና የክልል እንዲሁም ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች መገኘታቸውን ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም