አፍሪካዊያን የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት እንዲሰሩ ጥሪ ቀረበ

70

ሃምሌ 16/2013 (ኢዜአ)የቀድሞው የኢፌ.ዴ.ሪ. ጠ/ሚኒስትር አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ አፍሪካዊያን የተባበሩት መንግስታተ የዘላቂ ልማት ግቦችን ለማሳካት በተሻለ ፍጥነት መስራት እንዳለባቸው ገለፁ፡፡

በኬንያ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ለኢዜአ በላከው መረጃ እንዳስታወቀው፤ የአፍሪካ የአረንጓዴ አብዮት ጥምረት የቦርድ ሊቀመንበር አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ዛሬ በናይሮቢ ከድርጅቱ አጋሮች ጋር ባደረጉት ስብሰባ 20 በመቶ የሚሆኑ አፍሪካዊያን የምግብ ዋስትናቸው የተረጋገጠ አይደለም ብለዋል::

በዚህም የአካባቢው የአየር ንብረት ለውጥም ትልቅ እንቅፋት በመፍጠሩ አህጉሪቱ ለድርቅ ለጐርፍና ለሌሎች ችግሮች መጋለጧን ጠቅሰዋል፡፡

አፍሪካ የ2063 አጀንዳን ግብ እንድትመታና የየአገራቱ ዋና ዋና የግብርና ኘሮግራሞች እንዲሳኩ መንግስታት እና አጋሮች መተባበር ብቻ ሳይሆን ጥረታቸውን በእጥፍ መጨመር ይኖርባቸዋል ሲሉ አቶ ኃ/ማርያም ተናግረዋል፡፡

የአረግጓዴ ጥምረቱ እ.ኤ.አ. ከመስከረም 6-10/2021 በርካታ የአፍሪካ መሪዎች የሚሳተፉበት ዓመታዊ ስብሰባ ሲሆን በናይሮቢ ከተማ የሚደረግ ይሆናል፡፡

በመድረኩ ላይ ለጋሾች፣ በኬንያ የሚገኙ የተለያዩ የአፍሪካ አምባሳደሮች ተሳትፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም