የሻሸመኔ ወጣቶች የህዳሴ ግድብ የውሃ ሙሌትን በማስመልከተ የድጋፍ ሰልፍ እያደረጉ ነው

71

ሀዋሳ፣ 16/2013 (ኢዜአ) በኦሮሚያ ክልል የሻሸመኔ ከተማ ወጣቶች የታላቁ ህዳሴ ግድብ የሁለተኛ ዙር የውሃ ሙሌትን በማስመልከት ድጋፍ ሰልፍ እያደረጉ ነው።

የከተማዋ ወጣቶች "ግድቡ ለወጣቶች፤ ወጣቶች ለግድቡ እኛ ወጣቶች የሀሳብና የተግባር አንድነታችንን ለታላቁ ህዳሴ ግድብ እናረጋግጣለን፣ ግድቡ የሁላችንም የክብር ምንጭ ነው፣ ግደቡ ህዝባችንን ከጨለማ ግርዶሽ የሚያወጣ ስለሆነ እንደአይናችን ብሌን እንጠብቀዋለን" የሚሉና ሌሎች መፈክሮችን በማስተጋባት ድምፃቸውን እያሰሙ ነው።

"ግድቡ ባዶ እግራቸውን ከአረብ ሀገራት የሚባረሩ ወጣቶችን ነፃ የሚያወጣ በመሆኑ በተባበረ ክንዳችን ከፍፃሜ እናደርሰዋለን"  ሲሉም ወጣቶቹ ድጋፋቸውን በመግለጽ ላይ ናቸው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም