የጋምቤላ ክልል ምክር ቤት 12ኛ መደበኛ ጉባኤ በመጪው ሰኞ ይጀመራል

111

ጋምቤላ ፤ ሐምሌ 16/2013 (ኢዜአ) የጋምቤላ ህዝቦች ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ምክር ቤት ስድስተኛ የስራ ዘመን 12ኛ መደበኛ ጉባኤ በመጪው ሰኞ እንደሚጀመር የምክር ቤቱ ጽህፈት ቤት አስታወቀ።

ጽህፈት ቤቱ ለኢዜአ በላከው መግለጫ እንዳመለከተው፤ ጉባኤው ከሐምሌ 19/2013 ዓ.ም ጀምሮ ለሶስት ቀናት በጋምቤላ ከተማ ያካሄዳል።

ጉባኤው በሚኖረው ቆይታ የ2013 በጀት ዓመት የልማትና የመልካም አስተዳደር ዕቅድ አፈጻጸም፣ የክልሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤትና ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤቶች የስራ ክንውን ሪፖርቶችን በማዳመጥ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ተገልጿል።

እንዲሁም የቀጣይ የተያዘው በጀት ዓመት የልማትና የመልካም አስተዳድር እቅድ፣ የማስፈጸሚያ በጀት ላይ ተወያይቶ እንደሚያጸድቅ በመግለጫው  ተመላክቷል።

ጉባኤው የተለያዩ ረቂቅ አዋጆችን ላይም ውይይት በማድረግ መርምሮ እንደሚያጸድቅ ይጠበቃል።

በመጪው ሰኞ በሚጀመረው ጉባኤው  የምክር ቤት አባላትን ጨምሮ ከ350 በላይ የክልል፣ የዞንና የወረዳ አመራሮች ፣የሀገር ሽማግሌዎችና የኃይማኖት አባቶች እንደሚሳተፉ ተገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም