በየመን ይኖሩ የነበሩ 132 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው ተመለሱ

46
አዲስ አበባ ነሀሴ 1/2010 ዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት በጦርነት ውስጥ በምትገኘው የመን ይኖሩ የነበሩ 132 ኢትዮጵያዊያን ወደ ሀገራቸው መመለሱን አስታወቀ። ኢትዮጵያዊያኑ በጦርነት ምክንያት ቀውስ ውስጥ ከምትገኘው የመን ወደሀገራቸው እንዲመለሱ የተደረገው በፍቃዳቸው መሆኑን ድርጅቱ ገልጿል። ኢትዮያዊኑን ከየመን መዲና ሰንኣ ወደ ሁዳይዳህ ከተማ ከተጓዙ በኋላ በጅቡቲ በኩል ወደ ሀገራቸው እንዲገቡ ድጋፍ ማድረጉን ነው ድርጅቱ ያስታወቀው። በፍቃዳቸው ወደ ሀገራቸው ለሚመለሱ ኢትዮዽያዊያን ስደተኞች የሚያደርገውን ድጋፍ እንደሚቀጥልም ድርጅቱ ጠቅሷል። 116 ሶማሊያዊያንም በፍቃዳቸው ከኤደን ከተማ እንዲወጡ ተደርጓል። በየመን 4ኛ ከተማ ሁዳይዳህና አቅራቢያዋ ባለው አለመረጋጋት ሳቢያ 100 ሺህ የመናዊያን የተፈናቀሉ ሲሆን በየቀኑ ለ500 ሰዎች የምግብ  እንዲሁም ለ200 ያህሎቹ ደግሞ የህክምና እርዳታ እያቀረበ መሆኑን ገልጿል።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም