በኢትዮጵያ ላይ የሚሞከረውን የውጭና የውስጥ ጫናዎች ለመመከት ሁሉም ኢትዮጵያዊ በአንድነት ሊቆም ይገባል...ምሁራን

63

ጋምቤላ፤ ሐምሌ 10/2013 (ኢዜአ) ኢትዮጵያን ለማፍረስ የሚሞከረውን የውጭና የውስጥ ጫናዎች ለመመከት ሁሉም ኢትዮጵያውያን በአንድነት መቆም ያለባቸው ጊዜ መሆኑን በጋምቤላ ዩኒቨርሲቲ አስተያየታቸውን ለኢዜአ የሰጡ ምሁራን ተናገሩ።

ምሁራኑ እንዳሉት፤ ምዕራባዊያን ጫና ለመፍጠር እየሞከሩ ያሉት ኢትዮጵያ የተፈጥሮ ሀብቷን አልምታ ከድህነት ለመውጣትና ጠንከራ መንግስት ለመገንባት በምታደረገው ጥረት ምክንያት ነው።

በሰላምና ደህንነት የሶስተኛ ዲግሪያቸውን የጠናቀቁት ምሁር ዶክተር ግዛቸው ተሾመ በሰጡት አስተያየት፤  አሁን ላይ የህወሃት አሸባሪ ቡድን ከውጪ ኃይሎች ጋር በተናበበ መልኩ ኢትዮጵያን ለማፍረስ እየሰራ ነው ብለዋል።

ኢትዮጵያውያን ሀገርን ለማፍረሰን የሚመጣን ኃይል የማሳፈር የቆየ ታሪካቸውን አሁንም ለመድገም በተባበር ክንድ ሊሰሩ እንደሚገባ ተናግረዋል።

አሸባሪው ቡድን ህፃናትን ለጦርነት አሰልፎ ምርዕራባዊን አይታው እንዳለዩ ዝም ማለታቸው ከፍተኛ ትዝብት ውስጥ የሚጥል መሆኑን ጠቁመው በመንግስት በኩል ይህ ተፈጽሞ ቢሆን   ምን ዓይነት ጫና ሊመፍጠር ይችል እንደነበር  መገመት እንደሚቻል ገልጸዋል።

ምዕራባዊያን በአፍሪካ ውስጥ የሚፈለጉት ለእነሱ የሚታዘዝ መንግስት መሆኑን የገለጹት ምህሩ በኢትዮጵያም ባለፉት 27 ዓመታት የነበረው መንግስት ይህኑ አሰራር የተከተል ነበር ብለዋል።

አሁን ላይ ምዕረባዊያን በኢትዮጵያ ጫና ለመፍጠር የሚያደረጉት ሙከራ የተፈጥሮ ሀብቷን በይቻላል መንፈስ በእሯሷ አቅም አልምታ ለመጠቀምና በማንም ተጽዕኖ ስር የማይወድቅ ጠንክራ ሀገረ መንግስት ለመገንባት ያላትን አቋም ከመገንዘብ የመነጨ መሆኑን አስረድተዋል።

በመሆኑም በጅንታው የህወሐት አሸባሪ ቡድንና በጪ ኃይሎች ኢትዮጵያን ለማፍረስ የተቃጠውን  አደጋ ለመመከት ሁሉም ኢትዮጵያውን የውስጥ አንድነቱ በማጠናከር ሊሰራ  እንደሚገባ ነው ምሁሩ የገለጹት።

በፖለቲካ ሳይንስና በዓልም አቀፍ ግንኙነት እንዲሁም በፌዴራሊዝም የአንደኛና ሁለተኛ ዲግሪያቸውን ያጠናቁት ምሁር  ሉል ደቪድ በበኩላቸው፤ አሸባሪው የህወሐት ቡድን እየወጋው ያለው እራሱ ያዘጋጀውን  ህገ መንግስት ነው ብለዋል።

መንግስት በህገ መንግስቱ አንቀጽ ዘጠኝ በተቀመጠው ድንጋጌ መሰረት የጀመረው ህግ የማስከበር ተግባር አግባብነት ያለውና በመላው ኢትዮጵያ ሊደገፍ የሚገባው ተግባር መሆኑን ገልጸዋል።

አሸባሪው ቡድን በአሁኑ ወቅት እየተጋጨ ያለው ከመንግስት ጋር ሳይሆን ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ጋር መሆኑን ጠቁመው የኢትዮጵያ ህዝብ የዚህን የሽብር ቡድን ሲራ ለማክሸፍ በአንድነት መቆም አለበት ብለዋል።

ምዕራባዊያን እየፈጠሩ ያለው ጫና ኢትዮጵያ ከድህነት በመወጣት እራሷን ለመቻል በምታደረገው ጥረት ምክንያት መሆኑን ገልጸው፤  የውስጥ ሰላሟን ለማስጠበቅ በምታደረገው ጥረትም ተገቢ ያልሆነ ጣልቃ ገብነት እየታየባቸው መሆኑን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም