የኤምባሲና ቆንስላ ጽህፈት ቤቶችን በግማሽ የመቀነስ እቅድ አለ -ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ

70

አዲስ አበባ፣ሰኔ 28 ቀን 2013 (ኢዜአ) ኢትዮጵያ በዓለም ላይ ያሉ የኤምባሲና ቆንስላ ጽህፈት ቤቶቿን በግማሽ ለመቀነስ ፍላጎት እንዳላት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ  ወቅታዊ ሁኔታን በሚመለከት ለምክር ቤት አባላት ማብራሪያ ሰጥተዋል።

በማብራሪያቸውም ኢትዮጵያ በአለም ላይ ከ60 የሚበልጡ ኤምባሲዎችና ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች አሏት ሲሉ ጠቅሰዋል።

እነዚህን ቆንስላ ጽህፈት ቤት ሃላፊዎች  በተሻለ አገራቸውን እንዲጠቅሙና የሪፎርም ስራዎች መሰራት አለበት ብለዋል።
በተለይ በቀጣይ ስልጣን የሚረከበው መንግስት በዚህ ላይ ትኩረት ሰጠቶ ቢሰራ ይሻላል ብለዋል።

በአለም ላይ ስለ ለአገራቸው የሚሰሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን ዲፕሎማት እንዳሉና እነሱን በአግባቡ መጠቀም እንደሚያስፈልግም ጠቁመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም