የሀዋሳ ከተማ እግር ኳስ ክለብ አዲሴ ካሳን አሰልጣኝ አድርጎ ሾመ

93
አዲስ አበባ ሃምሌ 30/2010 አዲሴ ካሳ የሀዋሳ ከተማ እግር ኳስ ክለብ አሰልጣኝ ሆነው ተሾሙ። ክለቡ ከሶስት ሳምንታት በፊት ከአሰልጣኝ ውበቱ አባተ ጋር ከተለያየ በኋላ ያለ አሰልጣኝ ቆይቷል። አዲሱ አሰልጣኝ የሀዋሳ ክለብን የተረከቡት የሁለት ዓመት የኮንትራት ውል ስምምነት በማድረግ መሆኑን ከክለቡ የተገኘው መረጃ ያመለክታል። አዲሴ ካሳ ረዳት አሰልጣኞቻቸውን ዛሬ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል። ላለፉት ሁለት ዓመታት በከፍተኛ ሊግ እየተወዳደረ የሚገኘውን ወልቂጤ ከተማን በአሰልጣኝነት የመሩት አዲሴ ካሳ በተጫዋችነት ዘመናቸውም በሀዋሳ ከተማ እና ህንፃ ኮንስራክሽን ተጫውተዋል። ሀዋሳ ከተማ በ2010 ዓ.ም የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 36 ነጥብ በመሰብሰብ ዘጠነኛ ደረጃን ይዞ ማጠናቀቁ የሚታወስ ነው።
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም