በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን የሁሉንም ምርጫ ክልሎች ውጤት ይፋ ማድረግ አልተቻለም --ምርጫ ቦርድ

63

አዲስ አበባ፤ ሰኔ 24 ቀን 2013 (ኢዜአ) በተለያዩ ምክንያቶች እስካሁን የሁሉንም ምርጫ ክልሎች ውጤት ይፋ ማድረግ አለመቻሉን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምጫ ቦርድ ገለጸ።

የቦርዱ ሰብሳቢ ብርቱካን ሚደቅሳ እንደገለጹት፤ በድምር መዘግየት፣ በትራንስፖርት ችግር እንዲሁም የፖለቲካ ፖርቲዎች አቤቱታ ባቀረቡባቸው የምርጫ ክልሎች ውጤት ወደ ማዕከል ተጠቃሎ አልደረሰም።በዚህም እስካሁን ምርጫ ከተደረገባቸው የምርጫ ክልሎች የ26ቱ ውጤት አለመድረሱን ተናግረዋል።

በጋምቤላ 2፣ በአፋር 7፣ በአዲስ አበባ 8፣ በኦሮሚያ 4፣ በአማራ 3፣ በደቡብ ክልል 2 የምርጫ ክልሎች ውጤቶች አለመድረሳቸውን ጠቅሰዋል።ለቦርዱ ውጤት አያድርሱ እንጂ ምርጫ ክልሎቹ በአካባቢያቸው የምርጫ ውጤት የተለጠፈ መሆኑን ሰብሳቢዋ ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም