የኦ ኤም ኤን የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የኦ ኤም ኤን የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር እየተካሄደ ነው
92
አዲስ አበባ ሀምሌ 29/2010 የአዲስ አበባ ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ የምርቃት ፣ የገቢ ማሰባሰቢያና ጃዋር መሃመድ በግልፅ አቀባበል የሚደረግበት ፕሮግራም በሚሊኒየም አዳራሽ እየተካሄደ ነው። ፕሮግራሙ በአባ ገዳዎችና በሃይማኖት አባቶች ምርቃት ተጀምሯል። በፕሮግራሙ ላይ የኦሮሚያ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ለማ መገርሳን ጨምሮ የሚዲያው ዋና ዳይሬክተር ጃዋር መሃመድና የመንግስት ባለስልጣናት ተገኝተውበታል። የአማራ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ንጉሱ ጥላሁን በፕሮግራሙ ላይ ለመታደም ተገኝተዋ። ከተለያዩ አካባቢዎች የተውጣጡ ወጣቶች፣ የሚዲያው አድማጮችና ደጋፊዎች የሆኑ ሰዎች በፕሮግራሙ ላይ ታድመዋል። ሚዲያውን በቀጣይ አጠናክሮ ለማስኬድ የሚያስችል ገቢ ከተለያዩ ባለሃብቶችና ድርጅቶች ቃል ይገባል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን እስካሁን ቃል የተገባ የገንዘብ መጠንም ይፋ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።