በትግራይ ክልል የአሸባሪው ሕወሃት ርዝራዥ በሚንቀሳቀስበት አካባቢ የሰብዓዊ ድጋፍ በሚያደርጉ ሰዎች ላይ ጥቃት ተፈጸመ

54

ሰኔ 18 ቀን 2013 (ኢዜአ) በትግራይ ክልል የአሸባሪው ሕወሃት ርዝራዥ በሚንቀሳቀስበት አካባቢ የሰብዓዊ ድጋፍ በሚያደርጉ ሁለት ኢትዮጵያን እና አንድ ስፔናዊት ላይ ጥቃት መፈጸሙን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ጥቃቱ አቢ አዲ በተባለ ስፍራ ድንበር የለሽ የሀኪሞች ቡድን ሰራተኛ በሆኑ ሰዎች ላይ በአሸባሪዉ ህወሃት የተፈጸመ ነው።

በዚህም መንግስት የተሰማዉን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለሟች ቤተሰቦች መፅናናትን ተመኝቷል።

መንግስት በተደጋጋሚ ለጋሽ እና እርዳታ አቅራቢ ድርጅቶች የፀጥታ እና የስጋት አካባቢዎች ላይ ለሰራተኞች ደህንነት ሲባል ማንኛውም እንቅስቃሴ በመከላከያና በፀጥታ አካላት ታጅበዉ ለዜጎች እንዲያደርሱ ሲመክር መቆየቱ ይታወሳል።

ይሁን እንጅ አልፎ አልፎ የተወሰኑ ሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ ሰጭ ድርጅቶች ከመንግስት እዉቅና ዉጭ ሲንቀሳቀሱ ይስተዋላል ይህም የከፋ ችግር እያስከተለ መሆኑ ተገልጿል።

የፖለቲካ ትርፍ ለማግኝት ንፁሃንን የሚቀጥፍ የአሸባሪዉ ህወሃት የተበታተኑ ሽፍታዎችን ለህግ ለማቅረብ መንግስት ዛሬም ህዝባዊነቱን ጠብቆ ለዜጎች ሰላም እና ለአገራችን ሉዐላዊነት ይሰራል ብሏል የዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር።

በአሸባሪው የሕወሃት ርዝራዥ ሀይል በትግራይ ክልል የተለያዩ ቦታዎች በንጹሃን ዜጎች ላይ ተደጋጋሚ ጥቃት እየደረሰ መሆኑን የክልሉ ጊዚያዊ አስተዳደር መግለጹ ይታወሳል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም