በምዕራብ ሸዋ ዞን በደንዲ 2 ምርጫ ክልል አቶ ሽመልስ አብዲሳ ድምጽ ከሰጡ በኋላ ችግኝ ተከሉ

75

ሰኔ 14 ቀን 2013 ( ኢዜአ) በምዕራብ ሸዋ ዞን በደንዲ 2 ምርጫ ክልል በጊንጪ 01 አስተዳደር ምርጫ ጣቢያ ተገኝተው ድምጻቸውን የሰጡት አቶ ሽመልስ አብዲሳ ችግኝ ተከሉ።

አቶ ሽመልስ ድምጽ ከሰጡ በኋላ በደንዲ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል ቅጥር ግቢ ውስጥ ችግኝ በመትከል አረንጓዴ አሻራቸውን አኑረዋል።

በዛሬው ዕለት በኦሮሚያ ክልል ከምርጫው ጎን ለጎን ከ83 ሚሊዮን በላይ ችግኝ እንደሚተከል የገለጹት አቶ ሽመልስ፤ በክልሉ ሶስተኛው የአረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብር ከተጀመረበት ጊዜ አንስቶ የዛሬውን ሳይጨምር ከ800 ሚሊዮን በላይ ችግኝ መተከሉን ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም