ሰድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ በዴሞክራሲያዊነቱ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው ነው... አቶ ታገሠ ጫፎ

73

አርባምንጭ ፤ ሰኔ 14/2013 (ኢዜአ) ሰድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ነፃ ፣ ዴሞክራሲያዊነቱና ፍትሃዊነቱ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው መሆኑን አቶ ታገሠ ጫፎ ገለጹ። ፡፡

አቶ ታገሠ ጫፎ በሚወዳደሩበት የአርባ ምንጭ ምርጫ ክልል ተገኝተው ዛሬ ድምጽ ሰጥተዋል፡፡

በዚህ ወቅት እንደተናገሩት፤ በሀገሪቱ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በሁሉም የልማት መስኮች  ከምንጊዜውም የተሻለ ለውጥ እያስመዘገበች ነው።

ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ  ነፃ፣ ዴሞክራሲያዊነቱና ፍትሃዊነቱ በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ያለምንም ተጽዕኖ ህዝቡ በነፃነት በነቂስ ወጥቶ ድምፅ እየሰጠ መሆኑ ኢትዮጵያዊያን የራሳቸውን ሃላፊነት በአግባቡ እየተወጡ መሆናቸው ማረጋገጫ ነው ብለዋል፡፡

በካርዳችን ዴሞክራሲን በእጃችን ደግሞ ኢትዮጵያን አረንጓዴ እያለበስን በመሆኑ ታሪካዊ ምርጫ ነው ሲሉም ተናገረዋል፡፡

በአርባ ምንጭ ምርጫ ክልል ጫሞ ቀበሌ ምርጫ ጣቢያ አምስት ተገኝተው ድምጻቸውን ከሰጡ በኋላ በተዘጋጀው ስፍራ ችግኝ በመትከል ለአረንጓዴ ልማት አሻራቸውን አኑረዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም