በሀገሪቱ የተለያዩ አካባቢዎች ምርጫው እየተካሄደ ነው

57

ሰኔ 14/2013 (ኢዜአ) ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ በሀገሪቱ ክልሎች የተለያዩ አከባቢዎች እየተካሄደ ነው

በቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል አሶሳ ፣ በኦሮሚያ ምዕራብ ወለጋ ዞን ግምቢ ከተማ በሲዳማ ሀዋሳ በደቡብ ወላይታ ዞን ዳሞት ረይዴ ፣ ድሬዳዋ ምርጫው ከተጀመረባቸው አከባቢዎች መካከል ይገኙበታል።


አሶሳ የሚገኘው የኢዜአ ሪፖርተር እንደዘገበው በከተማዋ  ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በተለያዩ የምረጫ ጠቢያዎች ታዛቢዎች ባለበት ከሮጆው ባዶ መሆኑን ከተረጋገጠ በኋላ መብዛት ያለው ህዝብ ተሰልፎ ተራውን በመጠባበቅ በተረጋጋ ሁኔታ ድምጹን ሲሰጥ ተመልክቷል።


መራጮችም ቀደም ብለው በቦታው በመገኘት ደምጽ ለመስጠት ላይ ይገኛሉ።


በማስተናገድ በኩል መጓተቶች ስላሉ የሰው ሃይል ተጨምሮ ፍጥነት ቢታከልበት ሲሉ መራጮች አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።


ከዚህ ቀደም የነበሩት ምርጫዎች በተለይ ድምጽ መስጪያ ሚስጢር  ቦታው ሸራ በመሆኑ በነፋስ ሲወዛወዝ ስለሚከፈት  ሚስጥር ለመደበቅ ይቸገር የነበረው አሁን ግን የተሻለና ምቹ መሆኑን ገልጸዋል 

በድሬዳዋ የድምጽ መስጫ ቁሶች በታዛቢዎች ፊት ተቆጥረው ዝግጁ ሆነው  ሂደቱ በሰላም እየተካሄደ መሆኑን ሪፖርተሮቻቸው ከስፍራው ዘግበዋል።

በድሬደዋ የከዚራ ቁጥር ሁለት ምርጫ ጣቢያ የአፍሪካ ህብረት፣ የምስራቅ አፍሪካ ስታንድ ባይ ፎርስ፣ ድሬ የተቀናጀ የማህበረሰብ ድርጅት የሚባል ሲቪክ ማህበር በታዛቢነት ተገኝተዋል።

ህዝቡ ድምጹን ለመስጠት ተራውን እየተጠባበቅ ይገኛል።

በወላይታ የዳሞት ወይዴ ምርጫ ክልል ሁለት የቢጠና ማዘጋጃ ምርጫ ጣቢያ አንደ ድምፅ መራጮች የመስጠት ሂደት እየተከናወነ መሆኑን ሪፖርተራቻችን ከስፍራው  ዘግቧል።

በምርጫ ጣቢያው የመጀመሪያው ድምጽ ሰጪ አቶ ጰጥሮስ በቀለ ከሌሊቱ 11 ሰዓት ጀምሮ ወረፋ መያዙን ገልጾ ቀዳሚ መራጭ በመሆኑ ደስታ እንደሚሰማው ተናግረዋል።

ከዚህ ቀደም በሁለት ምርጫዎች መሳተፋቸውን የገለጹት አቶ ጰጥሮስ በምርጫው ሂደት የታዘቡት ሥርዓትና ህዝቡ ከሌሊት ጀምሮ በመሰለፍ ለምርጫው ተሳትፎ ያሳዩት ቁርጠኝነት ተስፋ ሰጪ መሆኑን አመልክተዋል።

ሌላኛው አቶ ታከለ ለማ በበኩላቸው፤ ከሌሊቱ 11:30 ጀምሮ በጉጉት ስጠብቅ የነበረውን ምርጫ መፈጸማቸውን አስረድተዋል።

የድምፅ አሰጣጥ ሂደት ገለጻ መደረጉንና ካለምንም ተጽዕኖ የፈለጉት ፓርቲ መምረጣቸውን ገልጸዋል።

ሂደቱ ከሌሎች የምርጫ ጊዜያት የተለየ መሆኑን ገልጸዋል።

በዚሁ የምርጫ ጣቢያ የተመዘገቡ 1 ሺህ 500 መራጮች ሲሆን በየተራ በመምረጥ ላይ ናቸው።

ሲዳማ ክልል የተለያዩ የምርጫ ክልልች በሚገኙ ጣቢያዎች ዛሬ 12 ሰዓት ጀምሮ በየምርጫ ጣቢያዎቹ የድምጽ መስጫ ወረቀቶች በታዛቢዎች ፊት ቆጠራ ከተደረገ በኋላ ድምጽ መስጠት ተጀምሮ ቀጥሏል።

በሀዋሳ ዲላ፣ አለታወንዶ፣ በንሳ ሾኔ ሚዛንና አርባምንጭና ወላይታ ሶዶ የሚገኙ የኢዜአ ሪፖርተሮች እንደዘገቡት መራጩ ከንጋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በየጣቢያዎች በመገኘት ሀዝቡ ድምጽ መስጠት ላይ ይገኛል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም