የቢሾፍቱ ነዋሪዎች ከማለዳው 12 ሠዓት ጀምሮ ድምጻቸውን እየሰጡ ነው

54

ቢሾፍቱ፤ ሰኔ 14/2013(ኢዜአ) የቢሾፍቱ ከተማ ነዋሪዎች ከማለዳው 12፡00 ሠዓት ጀምሮ በምርጫ ጣቢያዎች በመገኘት ድምጻቸውን በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

የምርጫ አስፈጻሚዎችና ታዛቢዎች ድምፅ መስጠት ከሚጀመርበት ሠዓት ቀደም ብለው በመገኘት አስፈላጊ ዝግጅቶችን ማጠናቀቃቸውን የኢዜአ ሪፖርተር አረጋግጧል።

የከተማዋ ነዋሪዎች ይበጀናል ለሚሉት የፖለቲካ ፓርቲ ድምጻቸውን በነፃነት እየሰጡ መሆኑንም በመርጫ ጣቢያዎች ተዘዋውሮ ተመልክቷል።

ምርጫውን ማንም ያሸንፍ ማን የኢትዮጵያን ዘላቂ ሠላም ማረጋገጥና የዜጎችን መሰረታዊ ፍላጎቶች ለማሟላት መስራት አለበት ሲሉ ድምፅ የሰጡ ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ተፎካካሪ ፓርቲዎችና መራጩ ሕዝብ የምርጫውን ውጤት በጨዋነት በመቀበል የኢትዮጵያን ቀጣይ እጣ ፈንታ የተሻለ ለማድረግ እንዲሰሩም ጥሪ አቅርበዋል።

በከተማዋ ብልጽግና፣ የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ /ኢዜማ/ እና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ /አብን/ ይወዳደራሉ።

በቢሾፍቱ ከተማ ከ83 ሺህ በላይ ዜጎች የምርጫ ካርድ ወስደዋል። 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም