''ብልፅግና ፓርቲን መምረጥ ሀገራዊ አንድነትና አብሮነትን መምረጥ ነው'' -የፓርቲው ከፍተኛ አመራር

58

አዳማ ሰኔ 9/2013 /ኢዜአ/ ''ብልፅግና ፓርቲን መምረጥ ሀገራዊ አንድነት፣ የህዝቦች ወንድማማቾችነትና አብሮነትን መምረጥ ነው'' ስሉ የፓርቲው የሞጆ ከተማ ከፍተኛ አመራር ገለፁ።

የፓርቲው የሞጆ ከተማ ጽህፈት ቤት የማጠቃላያ የምርጫ ቅስቀሳውን ዛሬ አካሂዷል።

በብልጽግና ፓርቲ የሞጆ ከተማ ጽህፈት ቤት ከፍተኛ አመራር ወይዘሮ መሰረት አሰፋ በሰልፉ ላይ  ባስተላለፉት መልእክት ''ብልፅግና ፓርቲ ሀገራዊ አንድነትን፣ የህዝቦች ወንድማማችነትና አብሮነት በዘላቂት የሚያስጠብቅ ነው''።

ሞጆ የሚመጥናት ልማትና ዕድገት እንዲኖራት ለማድረግ የሚያስችሉ ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት መስጫ መሰረተ ልማትቶች እየተከናወኑ መሆናቸውን ተናግረዋል'።

የመሰረተ ልማት ግንባታዎቹ የብልጽግና ፓርቱ በሳል አመራር ውጤቶች ማሳያዎች መሆናቸውን አመልክተዋል።

"የከተማው ህዝብ ማጣጣም የጀመረውን የልማት፣ የዕኩልነትና የነፃነት ቱሩፋቶችን በማስቀጠል ዘላቂ ተጠቀሚነቱን ለማረጋገጥ ብልጽግና ፓርቲን ይምረጥ" ሲሉ ጥሪ አቅርበዋል።

"በህዝቦች መካከል ለዘመናት  መጠራጠር እንዲፈጠር፣ አብሮነት፣ ወንድማማቾችነትና አንድነትን የሸረሸረው ሃይል በህዝብና በለውጡ አመራር ትብብር ተወግዶ የዕኩልነትና የነፃነት ተስፋ እያበበ ባለበት ወቅት 6ኛው ሀገራዊ ምርጫ መካሄዱ ታሪካዊ  ያደርገዋል" ብለዋል።

"የሞጆ ከተማ ህዝብ ለብልፅግና ፓርቲ ድምፁን በመስጠት የተጀመረው ሁሉን አቀፍ ለውጥ ከዳር እንዲደርስ በካርዱ መወሰን አለበት" ሲሉ ጥሪ አስተላልፈዋል።

"መራጩ ህዝብ  በነቂስ በመውጣት ለወኪሉ ድምጽ እንዲሰጥ መልእክት አስተላልፈዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም