የ2014 የበጀት ረቂቅ ዘላቂ፣ ፍትሃዊና ሁሉን አካታችን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማረጋጋጥ ያስችላል--የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ

48

ሰኔ 8/2013 (ኢዜአ) የ2014  የበጀት ረቂቅ ዘላቂ፣ ፍትሃዊና ሁሉን አካታችን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማረጋጋጥ በሚያስችል መልኩ የተዘጋጀ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስትሩ አህመድ ሺዴ ገለጹ፡፡

ሚንስትሩ ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የ2014 የስራ ዘመን የበጀት ረቂቅ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርበዋል፡፡

በዚሁ ወቅት እንደገለጹት የመንግስት ወጭ በፍኖተ ብልጽግና ጽንሰ ሀሳብ ቅድሚያ በተሰጣቸው የሀገሪቱን ብልጽግና ለማረጋገጥ ለሚረዱ ለማህበራዊና ኢኮኖሚ ዘፎች ልማት ማስፈጸሚያ እንዲሆን ታስቦ የተዘጋጀ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በጀቱ  ዘላቂ፣ ፍትሃዊና፣ ሁሉን አካታች የኢኮኖሚ እድገት እንዲረጋገጥና የተረጋጋ ማክሮ ኢኮኖሚ እንዲሰፍን በሚያስችል መልኩ ይተገበራል ብለዋል፡፡

የመንግስት የወጪ ፖሊሲ የሰው ሃብት ልማት፣ የመሰረተ ልማትን ማስፋፊያና ለአምራች ዘረፎች ምርታማነት ማሳደግ ላይ ትኩረት ማድረጉን የሚቀጥል መሆኑን አስረድተዋል፡፡

ይህም ፍትሃዊ፣ ሁሉን አቀፍ በሆነ መልኩ የሚተገበር ሲሆን በተጨማሪም ለአዳዲስ እድገት ተኮር ዘረፎች በከፍተኛ ሁኔታን ከግምት ያስገባ በጀት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

 የመንግስት በጀት ጉደለት አሸፋፋን በተመለከተ የዋጋ ንረትን በማያስከተልና በቅርቡ  በተቋቋመው የቲሬዥሪ ገበያ በመጠቀም በሚወሰድ በድር ላይ በመመሰረት ይሆናል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የመንግስት  ወጪ በጀት የተዘጋጀው የመንግስትን የፋይናስ አቅም ከግምት በማስገባት መስራቤቶች ተልእካአቸውንና ኃላፊነታቸውን ከማሳካት አንጻርና እቅዶቻቸውን ውጤታማ በሆነ መልኩ ለመፈጸም እንዲያስችላቸው ከግምት በማስገባት እንደሆነ አንስተዋል፡፡

ከዚህም በተጨማሪም ለዋና ዋና ተገባሮችና ለፖሮጀክቶች የሚያስፈልገው ውጪዎችን በመገምገም  ግበአትን ከውጤት ጋር የሚያዛምድ ተጠያቂነትን በሚያሰፈን መልኩ የተዘጋጀ መሆኑን አብራርተዋል፡፡

በ2014 የበጀት አመት የኑሮ ውደነቱን ወደ አንድ አኃዝና የኢኮኖሚ ዕደገቱንም በ8.7 በመቶ ለማሳደግ መታቀዱን ገልጸዋል፡፡

የዘንድሮ አመት የኢኮኖሚ እድገት 6.1 መሆኑም ተነግሯል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም