ናፍታሊ ቤኔት 13ኛው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ቃለ መሐላ ፈጸሙ

72

ሰኔ 07 /2013 (ኢዜአ) ናፍታሊ ቤኔት በእስራኤል 36ኛ መንግስት አስራ ሦስተኛው የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ቃለ መሐላ ፈጸሙ።

ናፍታሊ ቤኔት ቃለ መሐላ በመፈጸም የጠቅላይ ሚኒስትርነት ስልጣናቸውን ከኔታንያሁ ተረክበዋል።

ያኢር ላፒድ ደግሞ ተለዋጭ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በመሆን ቃለ መሐላ መፈጸማቸው ታውቋል።

ለ12 ዓመታት እስራኤልን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ያገለገሉት ቤኒያሚን ኔታንያሁ የተቃዋሚ ፓርቲው የሊኩይድ ፓርቲ መሪ ይሆናሉ ተብሏል።

የያሚና ፓርቲ መሪ ቤኔት እስከ መስከረም 2023 ድረስ ጠቅላይ ሚኒስትር በመሆን ይቆያሉ ነው የተባለው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም