የኢትዮጵያ መንገድ ፈንድ ጽህፈት ቤት 21 ሞተር ግሬደሮችን ለክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች አስረከበ

102

አዲስ አበባ፣ ግንቦት 29/2013 ( ኢዜአ)  የኢትዮጵያ መንገድ ፈንድ ጽህፈት ቤት 21 ሞተር ግሬደሮችን ለክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች አስረከበ።

የሞተር ግሬደሮቹ 600 ሚሊዮን ብር ወጭ የተደረገባቸው ሲሆን ለክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች ለመንገድ ጥገና አገልግሎት እንዲውሉ ታስቦ የቀረቡ ናቸው ተብሏል።

በርክክብ ሥነ ስርዓቱ ላይ የትራንስፖርት ሚኒስትሯ ዳግማዊት ሞገስ፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤ አደም ፋራህና ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሃላፊዎች ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ መንገድ ፈንድ ጽህፈት ቤት ለመንገዶች ጥገና እና ደህንነት የሚውሉ ወጭዎችን ለመሸፈን ታልሞ በአዋጅ ቁጥር 66/1989 በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የተቋቋመ የመንግስት መስሪያ ቤት ነው።

የመንገድ ጥገና የማያቋርጥ የገንዘብ ፈሰስ የሚጠይቅ በመሆኑ ተቋሙ እንዲቋቋም የተደረገ ሲሆን በዚህም በተያዘው በጀት ዓመት የመጀመሪያው ስድስት ወር 1 ነጥብ 4 ቢሊዮን ብር ገቢ መሰብሰቡ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም