በሱማሌ ክልል ደገሀቡር ከተማ ዘመናዊ ስቴዲዬም ሊገነባ ነው

80

አዲስ አበባ ግንቦት 28 / 2013 (ኢዜአ) በሱማሌ ክልል ደገሃቡር ከተማ በ40 ሚሊዮን ብር ዘመናዊ ስቴዲዬም ሊገነባ ነው።

የሱማሌ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር አቶ ሙስጠፌ መሐመድ ለስቴዲዬሙ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ አስቀምጠዋል።

ስቴዲየሙ በአጠቃላይ 20 ሺህ ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ቦታ ላይ የሚገነባ ይሆናል።

ግንባታውም 40 ሚሊዮን ብር ወጪ የሚጠይቅ ሲሆን፤ በሁለት ዓመታት ውስጥ ለማጠናቀቅ እቅድ ተይዞለታል።

ስቴዲዬሙ 20 ሺህ ተመልካች የመያዝ አቅም እንዲኖረው ሆኖ እንደሚገነባም የስፖርት ኮሚሽን መረጃ ያመለክታል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም