የሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተመረቀ

82

ሰመራ፣ ግንቦት 07 /2013 (ኢዜአ) ግንባታው በ2 ሺህ 140 ሄክታር መሬት ላይ ያረፈው የሰመራ ኢንዱስትሪ ፓርክ ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ተመረቀ።

ፓርኩ ከአጠቃላይ ይዞታው በመጀመሪያው ምዕራፍ የግንባታ ሥራው የተጠናቀቀውና በ50 ሄክታር መሬት ያረፈ ነው።

በፓርኩ የመጀመሪያ ምዕራፍ ግንባታ ስምንት ማምረቻ ሼዶች የተገነቡ ሲሆን እያንዳንዳቸው 5 ሺህ 500 ካሬ ሜትር ስፋት እንዳላቸው ታውቋል።

ሼዶቹ በዋናነት ከጥጥ ጀምሮ ጨርቃ ጨርቅና አልባሳት፣ ቆዳና የቆዳ ውጤቶች እንዲሁም በተለያዩ ማኑፋክቸሪንግ ዘርፎች ላይ ለመሰማራት የሚያስችሉ ናቸው።

የኢንዱስትሪ ፓርኩ ለጅቡቲ ወደብ ካለው ቅርበት አንጻር የኢትዮጵያን የወጪ ንግድ ያሳልጣል ተብሎ ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም