ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝደንት ጋር ተወያዩ

93

ሚያዚያ 28/2013 (ኢዜአ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን ከደቡብ አፍሪካ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት ሲሪ ራማፎዛ ጋር በፕሪቶሪያ ተገናኝተው በሁለቱ አገሮች የሁለትዮሽ እና ቀጠናዊ ጉዳዮች ላይ ፍሬያማ ወይይት አድርገዋል።

በውይይታቸው በኢትዮጵያ ያለው ወቅታዊ ጉዳዮች በተመለከተ ገለፃ አድርገውላቸዋል ።

በትግራይ ክልል ህግ የማስከበር እርምጃን ተከትሎ የሰብዓዊ እርዳታ ድጋፍ በስፋት ተደራሽ እየተደረገ መሆኑን አቶ ደመቀ ገልፀዋል።

ከሰብአዊ መብት ጋር በተያያዘ የሚነሱ ጥሰቶችን በመመርመር ተጠያቂ የሆኑትን ለሕግ ለማቅረብ መንግሥት ያለውን ቁርጠኝነት እና የተሰሩትን ስራዎች በዝርዝር ገልፀዋል።

የህዳሴ ግድብን አስመልክቶ በአፍሪካ ህብረት መሪነት የሶስትዮሽ ወገን ድርድር እንዲቀጥል ኢትዮጵያ ያላትን ፅኑ አቋም አሰረድተዋል።

ስድስተኛው ሀገራዊ ምርጫ በተሳካ መልኩ ለማካሄድ የሚያስችሉ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች በትኩረት እየተከናወኑ መሆኑን አመልክተዋል።

አቶ ደመቀ ፕሬዝዳንት ራማፎዛ ለአፍሪካውያን ችግር አፍሪካዊ መፍትሔ መፈለግ መርሀ በማራመድ ላሳዩት የመሪነት ሚና አድናቆታቸውን ገልጸዋል።

(የውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር)

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም