አራተኛው የኢትዮጵያ ፓትርያርክ ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስ አዲስ አበባ ገቡ

59
ሐምሌ 25/2010 አራተኛው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ በጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስና ብጹአን ሊቃነ ጳጳሳት አዲስ አበባ ገቡ፡፡ የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶክተር ዐቢይ አህመድ በተገኙበት የሀይማኖት አባቶች እርቀ ሰላም ማውረዳቸው ይታወሳል፡፡ ይህን ተከትሎም ለ26 ዓመታት በስደት ላይ የነበሩትን በጹዕ ወቅዱስ አቡነ መርቆሬዎስን ጨምሮ ሊቃነ ጳጳሳት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ ጋር ዛሬ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ የሀይማኖት አባቶች፣ የእምነቱ ተከታዮችና የመንግሥት የስራ ኃላፊዎች ቦሌ ዓለም ዓቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተገኝተው አቀባበል እያደረጉላቸው ነው፡፡ በመንበረ ጸባዖት ቅድስት ስላሴ ካቴድራል ቤተክርስቲያንም ደማቅ የአቀባል ስነ ስርዓት ይደረግላቸዋል፡፡ የፊታችን ቅዳሜ በሚሊኒየም አዳራሽ ሁለተኛ የእርቀ ሰላም ዝግጅት እንደሚኖር ተነግሯል፡፡ በዝግጀቱ ላይ ሁለቱ ፓርትርያርኮችና ሌሎች አባቶችና ምዕመናን እንዲሁም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ፣ አምባሳደሮችና ሌሎች የመንግስት ኃላፊዎችን ጨምሮ 25 ሺህ ታዳሚዎች ይገኛሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም