ጭንቀት እራስን እስከማጥፋት ላልተገባ ወሳኔ ስለሚዳርግ ትኩረት ልንሰጠው ይገባል- የስነ አእምሮ ምህራን

143

ጅማ መጋቢት 10/2013 (ኢዜአ) ጭንቀት እራስን ለመጥፋት ምክንያት ሊሆን ስለሚችል ለጉዳዩ ትኩረት ልንሰጠው ይገባል ሲሉ የስነ አእምሮ ምህራን አስገነዘቡ፡፡

በጅማ ዩኒቨርስቲ የስነ አህምሮ ህክምና ክፍልና በነፀብራቅ ቲያትርና ሮቦት ሚዲያ ግሩፕ ትብብር የተዘጋጀ የአህምሮዊ ጤና የግንዛቤ የሚሰጥ መድረክ ዛሬ ተካሂዷል።

መድረኩ’’ ለመኖር ብዙ ምክንያቶች አሉን’’ በሚል መሪ ቃል የተዘጋጀ ሲሆን የጅማ ዩኒቨርሲቲ ወጣቶችን የሳተፈ የኪነ-ጥበብ ዝግጅት ተካሂዶበታል።

’’ለመኖር ምክንያቱ ብዙ ነው፣ ከመሰናበት መሰንበት ይሻላል፣ያልታመመ አእምሮን እናክም’’ የተሰኙ መልእክች በመድረጁ ተላልፈዋል።

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የጅማ ዩኒቨርሲቲ የስነ አእምሮ ትምህርት ክፍል ባልደረባ ሲስተር ወርቅነሽ ተሰማ“ለአእምሮ ጤና ትኩረት ሊሰጠው ይገባል” ብለዋል።

የጅማ ዩኒቨርሲቲ የስነ አእምሮ ሃኪም ዶክተር አለማየሁ ነጋሽ በበኩላቸው “አእምሮውን የታመመ ሰው መታመሙን ማወቅ ስለማይችል ህክምናው ከማህበረሰብ መጀመር ይኖርበታል”ሲሉ ተናግረዋል። 

“በዚህ መልኩ ለችግሩ ትኩረት ተሰቶት ካልተሰራ ጭንቀት በተለይም ወጣቶችን እራስን እስከማጥፋት ለደረሰ ላልተፈለገ ውሳኔ ይዳርጋቸዋል” ብለዋል።

በከተማዋ ባለፉት ሁለት ወራት ወጣቶች በተደጋጋሚ እራሳቸውን ማጥፋታቸውን የተመለከተ ሪፖርት ይቀርብ እንደነበር የገለጹት ደግሞ የጅማ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ዲቪዥን ሀላፊ ዋና ኢኒስፔክተር ገዛኸኝ አውግቸው ተናግረዋል፡፡ 

አሁን ላይ የነበረዉ ሁኔታ መሻሻል ያለዉ መሆኑንና በቅርቡ መሰል ሪፖርት እንደሌለ ዋና ኢኒስፔክተሩ ገልጸዋል፡፡

የተዘጋጀው መድረክ ይህንኑ መነሻ ያደረገ እንደሆነ በስነ ስርአቱ ተነስቷል፡፡

በመድረኩ የተጋበዙ የስነ አህምሮ፣ የስነልቦናና የኪነጥበብ ባለሞያዎች ለወጣቶች ተስፋ የሚፈነጥቁና አነቃቂ መልክቶችን አስተለልፋዋል።

የኪነጥበብ ክበብ አባላት በመድረኩ አዝናኝ እና አስተማሪ ዝግጅቶችን አቅርበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም