ኢትዮ-ቴሌኮም የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ ኢንተርኔትን በደቡብ ደቡብ ምዕራብ አስጀመረ

63

ሚያዚያ 7/2013 ( ኢዜአ) ኢትዮ-ቴሌኮም የአራተኛው ትውልድ (4ጂ) ኤል.ቲ.ኢ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎትን በደቡብ  ደቡብ ምዕራብ ሪጅን አስጀመረ፡፡

ኩባንያው በደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ስድስት ከተሞችን ተጠቃሚ ያደረገ የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎትን ዛሬ በወላይታ ሶዶ ከተማ በይፋ አስጀምሯል፡፡

በአገልግሎቱ የወላይታ ሶዶ ከተማን ጨምሮ አርባ ምንጭ፣ ሆሳዕና፣ ቡታጅራ፣ ወልቂጤና ጅንካ ከተሞች የአገልግሎቱ ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡

ኢትዮ ቴሌኮም የአዲስ አበባ፣የደቡብ ምስራቅ ሪጅን፣ የሰሜን ምዕራብ ሪጅን እና የምስራቅ ምስራቅ ሪጅን ደንበኞቹን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ ማድረግ መቻሉ የሚታወስ ነው፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም