ግብረ ሃይሉ ለታላቁ ህዳሴ ግድብ ከ60 ሺህ ዶላር በላይ ድጋፍ አደረገ

110

ሚያዝያ 07 /2013 (ኢዜአ) በሳክራሜንቶ አካባቢ የሚገኘው የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ገንዘብ አሰባሳቢ ግብረ-ሃይል ከ60 ሺህ ዶላር በላይ በሎሳንጅለስ ለሚገኘው የኢትዮጰያ ቆንስላ አስረክቧል፡፡

የቆንስላ ጽህፈት ቤቱ ሃላፊ አምባሳደር ሙሉጌታ ከሊል ለተደረገው የገንዘብ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

እንደ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር መረጃ ድጋፉ በሌሎች የልማት ስራዎችም ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም