የሠላም ሚኒስቴር ለሠራተኞቹ የደንብ ልብስ አዘጋጀ

224

ሚያዚያ 6/2013 (ኢዜአ) የሠላም ሚኒስቴር ለሠራተኞቹ ያዘጋጀውን የደንብ ልብስ አስተዋወቀ።

ከደንብ ልብሱ በስተጀርባ የተቋሙ እሴት እውን እንዲሆን አገርና ሕዝብ ብዙ እንደሚጠብቁ ሚኒስትሯ ሙፈሪሃት ካሚል ገልፀዋል።

የመስሪያ ቤቱን መቋቋም ተከትሎ እየተከናወኑ ከሚገኙ የተቋም ግንባታ ስራዎች መካከል ጥናትን መሰረት ያደረገው የሠራተኞች የደንብ ልብስ አንዱ ነው።

የደንብ ልብሱ ሠራተኛውን ለላቀ የስራ ተነሳሽነትና ውጤታማነት እንዲተጋ የሚያደርግና ለተገልጋዮች ያለውን ክብርም የሚያጎላ ነው ሲሉ ሚኒስትሯ ገልፀዋል።

ሚኒስትር ሙፈሪያት ከደንብ ልብሱ በስተጀርባ ያለውን ምስጢር መረዳትና መተግበር 'ትልቁ ሸክማችን ነው' ብለዋል።

የደንብ ልብስ ለሠላም ግንባታ ተቋማት ወሳኝና ዓርአያ ነው ያሉት ሚኒስትሯ በቀጣይ የሚኒስቴሩ ተጠሪ ተቋማትም ይህንኑ ተግባራዊ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

የተቋሙ ሠራተኞች የደንብ ልብሳቸውን በመልበስ ቃለ መሃላ ፈጽመዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም