ካርድ ለማውጣት ነገ አትበሉ፤ ነገ ከዛሬ ይጀምራል -- ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ

69

ሚያዚያ 6 ቀን 2013 (ኢዜአ) “ካርድ ለማውጣት ነገ አትበሉ፤ ነገ ከዛሬ ይጀምራል” ሲሉ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ መራጮች የምርጫ ካርድ በጊዜ እንዲወስዱ አስገነዘቡ።

6ኛው ብሔራዊ ምርጫ ሊከናወን ጥቂት ሳምንታት እንደቀሩት ያስታወሱት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ “ዜጎች የመምረጥ ዴሞክራሲያዊ መብታቸውን በመጠቀም ንቁ ተሳትፎ እንዲያደርጉ ይጠበቃል” ብለዋል።

“የሕገ መንግሥታችን አንቀጽ 38 ሁሉም ኢትዮጵያዊ የመምረጥና የመመረጥ መብት እንዳለው ይደነግጋል” በማለት ገልጸው፤ “የሀገራችንን የነገ ዴሞክራሲ ለመወሰን፣ ዛሬ የመራጮች ምዝገባ መታወቂያ ካርድ እናውጣ።

ካርድ ለማውጣት ነገ አትበሉ፤ ነገ ከዛሬ ይጀምራል” ሲሉ መራጮች የምርጫ ካርድ እንዲወስዱ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

የመራጮች ምዝገባ መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን እስከ ሚያዝያ 15 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም