አቶ ደመቀ መኮንን ከዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ጋር ተወያዩ

72

ሚያዝያ 6 / 2013 (ኢዜአ) ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትርና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ደመቀ መኮንን የዓለም ጤና ድርጅት የአፍሪካ ዳይሬክተር ከሆኑት ከዶ/ር ማቲሺድሶ ሞኤቲ ጋር በጤናው ዘርፍ ጉዳዮች ተወያይተዋል።

በውይይቱ በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ እየተተገበረ ያለው የጤና ኤክስቴሽን ፕሮግራም ውጤታማ መሆኑን አቶ ደመቀ አስረድተዋል፡፡

የኮቪድ -19 ተፅዕኖን ለመቀነስና በሽታውን ለመከላከል መመሪያ ተዘጋጅቶ ተግባራዊ በመደረግ ላይ መሆኑንም ገልጸዋል።

ዳይሬክተሯ በበኩላቸው ኢትዮጵያ ከዓለም ጤና ድርጅት ጋር የረጅም ጊዜ አጋርና የትኩረት አገር መሆኗን ጠቅሰው፤ ድርጅቱ በጤና ዘርፍ ያለውን ትብብር የበለጠ ለማጠናከር ያላቸውን ፍላጎት መግለጻቸውን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ጽ/ቤት አስታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም