በመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን ማዕከል ውስጥ ለሚገኙ 200 አረጋዊያን የኮቪድ-19 ክትባት ተሰጠ

71

ሚያዚያ 6 /2013 (ኢዜአ) በመቄዶንያ የአረጋውያንና የአእምሮ ህሙማን ማዕከል ለሚገኙት እድሜቸው ከ65 ዓመት በላይ ለሆኑ እንዲሁም ተጓዳኝ ህመም ላለባቸው 200 አረጋዊያን በዛሬው እለት የኮቪድ-19 ክትባት ተሰጠ።

በዛሬው እለትም የመጀመሪያ ዙር ክትባት ለ200 አረጋዊያን የተሰጠ ሲሆን ተጨማሪ 300 ሰዎች ክትባቱን እንደሚያገኙ ይጠበቃል።

ማእከሉ በ2004 ዓ.ም የተቋቋመ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከ4 ሺህ በላይ ሰዎችን ከጎዳና ላይ በማንሳት እየተንከባከበ ይገኛል።

ማእከሉ ከአዲስ አበባ በተጨማሪ በኦሮሚያ፣ በአማራና ትግራይ ክልሎች ቦታ በመረከብ ረዳት የሌላቸውን አቅመ ደካሞች በመመገብና በመንከባከብ ላይ ይገኛል።

በአዲስ አበባ ብቻ እስካሁን ከ72 ሺህ 646 በላይ የህክምና ባለሙያዎችና ለኮቪድ-19 ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ክትባቱን መውሰዳቸው ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም