በክልሉ መጪው ምርጫ ሰላማዊና ዴሞክራሲዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ ወጣቶች ጠንክረው ሊሰሩ ይገባል-አቶ ኡሞደ ኡጀሉ

68

ጋምቤላ ፤ ሚያዚያ 4/2013 (ኢዜአ) የኮሮና ወረርሽኝን በመከላከል ስድስተኛ ጠቅላላ ምርጫ ሰላማዊና ዴሞክራሲዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የወጣቶች ሊግ አባላት ጠንክረው ሊሰሩ እንደሚገባ የብልጽግና ፓርቲ የጋምቤላ ክልል ከፍተኛ አመራር አቶ ኡሞደ ኡጀሉ አሳሰቡ።

የብልጽግና ፓርቲ  ወጣቶች ሊግ ዛሬ በጋምቤላ ከተማ የምርጫ ቅስቀሳ አካሄዷል።

በቅስቀሳው ስነ-ስርዓት የተገኙት አቶ ኡሞድ  እንዳሉት፤ የዘንድሮው ምርጫ  ከዚህ በፊቱ ከተካሄዱት ሁሉ ፍጹም ተአማኒ፣ ሰላማዊና ዴሞክራሲዊ የሆነ እንዲጠናቀቅ አስፈለጊው ዝግጅት ተደርጓል።

ፓርቲው በወንድማማችነት ላይ የመሰረተ ህብር ብሄራዊ አንድነትንና ዘላቂ ሰላም የተረጋገጠባት ኢትዮጵያን የመገንባት ከፍ ያለ ራዕይ ሰንቆ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል።

ፓርቲው የሚመራው መንግስት ባለፉት ሶስት ዓመታት የልማት የፕሮጀክት መሰረት ድንጋይ ማስቀመጥ ብቻ ሳይሆን በአጭር ጊዜ በማጠናቀቅ አሻራውን ለትውልድ የማስቀመጥ ስራ እንደጀመረ አስታውቀዋል።

ብልጽግና  የወጣቱ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያና ኢኮኖሚዊ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ በስብዕናና በሀገረ መንግስት ግንባታ የድርሻውን እንዲወጣ ጥረትእያደረገ እንሚገኝም ገልጸዋል።

ፓርቲው ባሳለፋቸው ዓመታት የውስጥና የውጭ ፀረ- ሰላም ኃልሎችን ሴራ በመመከት የተጀመረውን የብርሃን ጉዞ ይበልጥ ለማድመቅ አበክሮ እየሰራ እንደሚገኝ ተናግረዋል።

የኮሮና ወረርሽኝን በመከላከል ስድስተኛው ጠቅላላ ምርጫ ፍጹም ሰላማዊና ዴሞክራሲዊ ሆኖ እንዲጠናቀቅ የክልሉ ወጣቶች ሊግ አባላት  ጠንክረው ሊሰሩ እንደሚገባ አሳሰበዋል።

የብልጽግና ፓርቲ የጋምቤላ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ አመራር  አቶ ዶራር ኩም በበኩላቸው፤ለመጪው ሀገራዊና ክልላዊ ምርጫ ስኬት ከወጣቶች የላቀ ቁርጠኝነት እንደሚጠበቅ ገልጸዋል።

የብልጽግና ፓርቲ  ወጣቶች ሊግ የጋምቤላ ክልል ዋና ሰብሳቢ ወጣት ሯች ጎች መጪው ምርጫ ሰላማዊ ሆኖ  ከፍጻሜ እንዲደርስ ጠንክረው እንደሚሰሩ ገልጿል።

የወጣቱን ግንዛቤ በማሳደግ የሚፈልጋቸውን ዕእጩዎች እንዲመርጠም  የቅስቀሳ ስራ እንደሚያካሄዱ አስታውቋል።

በምርጫ ቅስቀሳው ፓርቲው ለክልልና ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረባቸው ዕጩዎች በተገኙበት  የፓርቲውን ማኒፌስቶና የመወዳደሪያ ምልክት ትውውቅ ስነ-ስርዓት ተካሄዷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም