ቴሌኮምን ወደ ግሉ ዘርፍ የማዞሩ ሂደት ለኢትዮጵያ መልካም ዕድሎችን ያነገበ ታላቅ የዲጂታል አጀንዳ ነው- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ

70

አዲስ አበባ ሚያዚያ 01 ቀን 2013 (ኢዜአ) ቴሌኮምን ወደ ግሉ ዘርፍ የማዞር ሂደት ለኢትዮጵያ የሚሰጡትን ዕድሎች እና የሀገሪቱን ታላቅ የዲጂታል አጀንዳ እውን ለማድረግ ያለመ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ ገለጹ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ ይህን የተናገሩት ከአፍሪካ ቴሌኮም ሪቪው ጋር ባደረጉት ቆይታ ነው።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቆይታቸውም ቴሌኮምን ወደ ግሉ ዘርፍ የማዛወሩ ሂደት ዋና ዓላማዎች የቴክኖሎጂ ፍሬዎችን በመጠቀም ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን በማሳደግ በሀገሪቱ ባለው ፍላጎት የተደገፉ መሆናቸውን አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ የመወዳደሪያ ተጠቃሚነት ባላት የአገልግሎት ኤክስፖርት፣ በማኑፋክቸሪንግ እና በግብርና ዘርፍ የአይሲቲ ዘርፉን ለመጠቀም መታቀዱንም ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ የአፍሪካ የብልጽግና ፋና ለመሆን አልማ እየሰራች ያለች አገር ነች ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ ይህንንም ራዕይ ሀገራዊ የአስር ዓመታት ዕቅዷ ታሳካዋለችም ብለዋል።

ቴሌኮምን ወደ ግል የማዘሩ ሂደት በዘረፉ የተሰማሩ ትልልቅ ዓለም አቀፍ አቅም ያላቸው ተቋማት የቴክኒካዊ እና የአሠራር ዕውቀትን ለመጠቀም ለኢትዮጵያ ትልቅ ዕድል እንደሚሰጥም ተናግርዋል።

ኢትዮጵያ፣ አይሲቲ እና ቴሌኮሙኒኬሽን በኢኮኖሚ እድገት እና የብልጽግና ዓላማዎችን ማስፈጸም የሚያስችል ግልጽ ራዕይ አላትም ብለዋል ጠቅላይ ሚኒስትሩ።

በኢትዮጵያ የተጀመረው ቴሌኮምን በከፊል ወደ ግል የማዘዋወር ሒደትም የሀገሪቷን የአዲስ ዘመን ጅማሮ ማሳያ መሆኑን ገልጸዋል።

በኢትዮጵያ ቴሌኮምን በከፊል ወደ ግል የማዘዋወር ሒደት ዋነኛው ዓላማ ሀገሪቱ የቴክኖሎጂ ዕድሎችን በመጠቀም የኢኮኖሚ ዕድገቷን ለማሳለጥ ካላት ፍላጎት የመነጨ መሆኑንም ነው የገለጹት።

እንደዘገባው ከሆነ ኢትዮጵያን የብልጽግና ጎዳና ላይ ሊያደርሳት የሚችል ጠንካራ የዲጂታል ስትራቴጂን በመጠቀም እየሠራች ያለች እና በፍጥነት እያደጉ ከሚገኙ የአፍሪካ አገራት አንዷ ነች።

ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025ን በማስጀመር ዲጂታል ስትራቴጂ ለኢትዮጵያ ሁሉን አቀፍ ብልጽግ እና የአተገባበር ህጎችን እና ተቋማዊ መዋቅሮችን መጽደቁን የተናገሩት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፤ "እኛም በኢትዮጵያ ውስጥ የንግድ ሥራ ቀላል እና የበለጠ የሚክስ ለማድረግ ቆራጥ እርምጃዎችን ወስደናል" ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም