የዓለም የስፖርት ቀን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ታስቦ ዋለ

66

አዲስ አበባ መጋቢት 2013 (ኢዜአ) የዓለም የስፖርት ቀን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የጤና እና አካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ በዛሬው እለት ታስቦ ዋለ።

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በ2005 ዓ.ም ስፖርት ለሰላም ልማት በሚል በየዓመቱ መጋቢት 28 ቀን ታስቦ እንዲውል ወስኗል።

ከዚህ ውሳኔ በኋላ ከ2006 ዓ.ም ጀምሮ በየመቱ በዛሬው እለት በተለያዩ መርሃ ግብሮች በተለያዩ የዓለም ሀገራት ይከበራል።

የእለቱ መከበር ዋነኛ ዓላማም ስፖርት ለሰላም፣ ለአብሮነት፣ ለልማት፣ ለጤናማ ህይወት ያለውን ጠቀሜታ ግንዛቤ ለመፍጠርና ለብዙዎች ለስፖርት ያላቸውን ግንዛቤ ለማሳደግ መሆኑ ይገለፃል።

እለቱን ምክንያት በማድረግም በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የጤና እና አካል ብቃት እንቅስቃሴ በማድረግ ታስቦ ውሏል።

ከግልና ከመንግስት መገናኛ ብዙሃን የስፖርት ጋዜጠኞችና የአካል ብቃት አሰልጣኞች በኢትዮጵያ ወጣቶች ስፖርት አካዳሚ ስፖርትዊ እንቅቃሴ አካሂዳዋል።

በእለቱ የኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኞች ማህበር ፕሬዚዳንት ጋዜጠኛ ንዋይ ይመር፣ የአካል ብቃት እንቀስቃሴ ባለሙያው ነጻነት ካሳ እና ሌሎች ባለሙያዎችም ተገኝተዋል።

የዓለም የስፖርት ቀን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለም አቀፍ ደረጃ ደግሞ ለ8ኛ ጊዜ ነው ዛሬ የተከበረው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም