የሀገር ውስጥ ባላሃብቶች በኢንደስትሪ ፓርኮች ያላቸው ድርሻን ለማሳደግ እየተሰራ ነው - ኢዜአ አማርኛ
የሀገር ውስጥ ባላሃብቶች በኢንደስትሪ ፓርኮች ያላቸው ድርሻን ለማሳደግ እየተሰራ ነው
100
መጋቢት 24/2013/ኢዜአ/ የሀገር ውስጥ ባላሃብቶች በኢንደስትሪ ፓርኮች ያላቸው ድርሻን ለማሳደግ እየተሰራ መሆኑን የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ገለጸ፡፡
ኮርፖሬሽኑ "የሃገር ውስጥ ባለሃብቶች በኢንደስትሪ ፓርኮች" በሚል ከሀገር ውስጥ ባላሃብቶች ጋር እየመከረ ነው፡፡
የኢንደስትሪ ፓርኮች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ሳንዶካን ደበበ እንዳሉት በኢንደስትሪ ፓርኮች የሃገር ውስጥ ባለሃብቶችን በማበረታታት ዓለም አቀፍ ገበያውን እንዲቀላቀሉ ቢታቀድም በሚፈለገው ደረጃ ውጤት አልመጣም፡፡
በኢንደስትሪ ፓርኮች ከሚገኙ ከ99 በላይ ባላሃብቶች የሃገር ውስጥ ድርሻ ከ15 በታች መሆኑንም ገልጸዋል።
በመሆኑም በቀጣይ ከውጭ ባላሃብቶች እኩልና ከዛም በላይ ድርሻ እንዲኖራቸው የተለያዩ ማበረታቻዎችን ለማድረግ እንደሚሰራም ገልጸዋል፡፡
በዛሬው ውይይት የሀገር ውስጥ ባለሃብቶችን በኢንደስትሪ ፓርኮች በሚፈለገው ደረጃ እንዳይሳተፉ እያጋጠማቸው ባሉ ተግዳሮቶች ዙሪያ ምክክር ይደረጋል፡፡
የኢንደስትሪ ፓርኮች ለ76 ሺህ በላይ ዜጎች የስራ ዕድል መፍጠራቸውን መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡