በቡሌ ሆራ ከተማ ህጻናትን የደፈረው ግለሰብ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት ተቀጣ

88

ነገሌ ፤ መጋቢት 23/2013( ኢዜአ) በምዕራብ ጉጂ ዞን ቡሌ ሆራ ከተማ ሶስት ህጻናትን በመድፈር ወንጀል የተከሰሰ ግለሰብ በ25 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የዞኑ ፖሊስ መምሪያ የሚዲያና ኮሙዩኒኬሽን ሃላፊ ዋና ሳጂን ፈዬራ  ኬይረዲን  እንደገለጹት፤ ካሳሁን አዳነ የተባለው ግለሰብ ህጻናቱ  በሚማሩበት  ትምህርት  ቤት በጥበቃ ስራ ላይ እያለ ጥፋቱን እንደፈጸመ በማስረጃ ተረጋግጦበታል፡፡

ፖሊስ ከህጻናቱ ወላጆች የደረሰውን ጥቆማ በመቀበል ድርጊቱ ከተፈጸመበት ከጥር 2013 ዓ.ም ጀምሮ ግለሰቡን  በቁጥጥር ስር አውሎ ከዐቃቢ ህግ  ጋር በመተባበር  ጉዳዩን  ሲመረምር መቆየቱን ተናግረዋል፡፡

ግለሰቡ ህጻናቱን ከደፈረ በኋላ ለወላጆቻችሁ  ብትናገሩ በቢለዋ አርዳችኋለው በማለት  ለተጨማሪ የአእምሮ ጭንቀት እንዲዳረጉ ማድረጉም በምርመራ ተረጋግጧል ብለዋል፡፡

ድርጊቱም  በሰው፣ ህክምና እና ሰነድ ማስረጃ  ተረጋግጦበት  ጥፋተኛ ሆኖ  በመገኘቱና  ሊከላከል ባለመቻሉ ጉዳዩን ሲከታተል የቆየው የዞኑ  ከፍተኛ ፍርድ ቤት መጋቢት 22/  2013 ዓ.ም በቡሌ ሆራ ከተማ በዋለው ችሎች የቅጣት ውሳኔውን ማስተላለፉን አስታውቀዋል፡፡

ከዚህ መጥፎ ተግባር ግንዛቤ በመውሰድ አሰሪዎች ሰራተኞቻቸውን ወላጆች ደግሞ ልጆቻቸውን በመከታተልና በመቆጣጠር ጥበቃና ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ዋና ሳጂን ፈዬራ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም