የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት በምርጫው ሂደት ላይ ተጽእኖ እንዳያሳድር ጥንቃቄ ማድረግ ያስፈልጋል ... የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች

63

መጋቢት 22/2013(ኢዜአ) የሃሰተኛ መረጃ ስርጭት በምርጫው ሂደት ላይ ተጽእኖ እንዳያሳድር ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚያስፈልግ የመገናኛ ብዙኃን ባለሙያዎች ተናገሩ።

ሁለተኛ ቀኑን የያዘው የአዲስ ወግ የውይይት መድረክ "የሃሰተኛ መረጃ በሰላማዊ ምርጫ ላይ ያለውን አሉታዊ ተጽእኖ እንዴት መግታት ይቻላል?" በሚል ርዕስ ውይይት እየተካሄደ ይገኛል።

በውይይቱ የመገናኛ ብዙኃን አካላትን ጨምሮ ሌሎችም ባለድርሻ አካላት በመሳተፍ ላይ ናቸው።

የመገናኛ ብዙኃን የሕግ ማሻሻያ ምክር ቤት ሰብሳቢ አቶ ሰለሞን ጎሹ እና ጋዜጠኛ ኤደን ብርሃኔ የመወያያ መነሻ ሃሳብ አቅርበዋል።

አቶ ሰለሞን በዚሁ ወቅት እንደገለጹት፤ ሃሰተኛ መረጃ በዘንድሮ ምርጫ ላይ ተጽእኖ እንዳያሳድር ከወዲሁ ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል።

ለዚህም የህግ ማዕቀፎችን ከማውጣት ጀምሮ ማህበረሰቡን ስለ ሃሰተኛ መረጃ ግንዛቤ እንዲኖረው የሚያደርግ አሰራር ሊኖር ይገባል ነው ያሉት።

ጋዜጠኛ ኤደን ብርሃኔ በበኩሏ የመረጃ ትክክለኛነትን ማረጋገጥ ላይ ትኩረት መደረግ አለበት ብላለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም