ብልጽግና ፓርቲ ይፋዊ የምርጫ ቅስቀሳውን ዛሬ በድሬዳዋ ጀመረ

63

ድሬዳዋ፤ መጋቢት 22/2013 (አዜአ) ብልጽግና ፓርቲ በድሬዳዋ ይፋዊ የምርጫ ቅስቀሳውን ዛሬ ጀምሯል።

ፓርቲው የማህበራዊ፣ፓለቲካዊና  የምጣኔ ሃብት ፓሊሲዎችና ስትራቴጂዎቹን በከተማው ዋና ዋና አደባባዮች በመዘዋወር እያስተዋወቀ ይገኛል።

ፓርቲው ድሬዳዋን የምስራቅ ኢትዮጵያ የኢንደስትሪ፣ የንግድና የአገልግሎት ማዕከል ለማድረግ የሰነቃቸውን መርሃ ግብሮች በቅስቀሳው ላይ አንስቷል ።

ለሁለት ሳምንታት በፓርቲው ሁለንተናዊ ጉዳዮች ላይ ስልጠና የተከታተሉት የፓርቲው አመራሮችና አባላት በምረጡኝ ቅስቀሳው ላይ ተሳታፊ ሆነዋል።

በቅስቀሳው ላይ የድሬዳዋ አስተዳደር ብልፅግና ፓርቲ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ መብራቴ ገብረየስን ጨምሮ የፓርቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ አባላትና ደጋፊዎችም እየተሳተፉ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም