ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ድሬዳዋ ገቡ

83

ኢመጋቢት 17 / 2013 (ኢዜአ) የኢፌዴሪ ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በሐሪሪ ክልልና ድሬዳዋ አስተዳደር የስራ ጉብኝት ለማድረግ ዛሬ ድሬዳዋ ገቡ።

ለፕሬዚዳንቷ የሐረሪ ክልል ርዕሰ መስተዳደር ኦርዲን በድሪ እና በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የድሬዳዋ አስተዳደር ንግድ፣ ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ቢሮ ሃላፊ አቶ ከድር ጁሃር ጨምሮ ሌሎችም የስራ ሃላፊዎች በድሬዳዋ አውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

ወደ ሐረሪ ክልል በማቅናትም ዛሬ በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ለሴቶች እየተደረገ ያሉ ሁለንተናዊ ድጋፎች፣ በሐረር ከተማ የሚገኘው የፌስቱላ ህክምና መስጫ ሆስፒታል እንደሚጎበኙ እንዲሁም የስብዕና ግንባታ ሆኖ የሚያገለገል ማዕከል ለመስራት የመሰረተ ድንጋይ እንደሚያስቀምጡ ይጠበቃል።

ነገ ደግሞ በድሬዳዋ ለሴቶች እየተደረገ ያሉ ድጋፎችን እንደሚመለከቱ ታውቋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም